ህጻናት እና ኤሌክትሮኒክስ

ህጻናት እንደ ላፕቶፕ፣ ታብሌት እና ስማርት ስልኮችን አዘውትረው የሚጠቀሙ ከሆነ ለተለያዩ የማህበራዊ እና የጤና ጉዳቶች ሊዳርጋቸው ይችላል። ይህም በህጻናቱ ላይ የትምህርት፣ የማህበራዊ ግንኙነት እና የባህሪ ችግር ሊ ያጋጥማቸዉ እንደሚችል የተለያዩ ጥናቶች ያመላክታሉ፡፡

1. የአእምሮ እድገት እክል

ህጻናት ከተወለዱ ጊዜ አንስቶ እስከ 21 ዓመታቸው ድረስ የአእምሯቸው እድገት ፈጣን ሲሆን፥ በዚህ የእድሜ ክልልውስጥ ያሉ ልጆች ጊዜያቸውን እንደ ላፕቶፕ፣ ታብሌት እና ስማርት ስልኮች የሚያሳልፉ ከሆነ የእምሯቸው ማደግ ፍጥነት ላይ እክል ሊገጥመው ይችላል። ለዚህም ዋነኛው ምክንያት ከእነዚህ ስልኮች ወይንም የኤሌክትሮኒክስ መሳርዎች የሚወጣው አደገኛ ጨረር በልጆች አእምሮ እድገት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ ስለሚኖረው ነው፡፡

2. የተዛባ የማህበራዊ ግንኙነት

ጊዜያቸውን እንደ አይፓድ፣ ታብሌት እንዲሁም ስማርት ስልኮች ላይ የሚያሳልፉ ልጆች በማህበራዊም ይሁን በትምህርት ህይወታቸው ላይ ከፍተኛ ችግር ሲያጋጥማቸው ይስተዋላል። ይህም የማህበራዊ ግኑኝነታቸው እና የስሜት መጎልበትን እድገት ከሰዎች ጋር ጊዜ በማሳለፍ ከሚኖራቸው ግኑኝነት እና መስተጋብር ጋር የሚቆራኝ ሲሆን በእነዚህ ኤሌክትሮኒክስ መሳርያዎች ላይ ጊዜአቸውን የሚያሳልፉ ልጆች ከሰዎች ጋር የሚኖራቸው ጊዜ ውስን ስለሚሆን ተገቢውን ክህሎት ከሌሎች ለመማር ጊዜውንና አጋጣሚውን አያገኙም፡፡

3. ከመጠን ያለፈ ውፍረት

ህጻናት ሙሉ ጊዜያቸውን እንደ ስማረት ስልክ፣ አየፓድ እና ኮምፒውተሮች ላይ ተቀምጠው የሚያሳልፉ ከሆነ የእለት ተእለት እንቅስቃሴያቸው አነስተኛ ስለሚሆን ከመጠን ላለፈ ውፍረት /Obesity/ በቀላሉ ሊጋለጡም ይችላሉ።

4. የእንቅልፍ ማነስ

ህጻናት በሞባይል ስልኮች ላይ ባሉ መጫወቻ ጌሞች አብዛኛውን ጊዜ የሚጫወቱ ከሆነ ከእንቅልፍ ይልቅ ጨዋታውን ስለሚመርጡ በእንቅልፍ እጦት ምክንያት ለተለያዩ ችግሮም ሊጋለጡ እና በአተኛኘታቸው ላይ ችግር ሊያጋጥማቸው እንደሚችል ጠናቶች ያመላክታሉ፡፡

5. ለጨረር መጋለጥ

ህጻናት የሞባይል ስልክም ይሁን ሌላ የኤሌከትሮኒክስ መገልገያ እቃዎችን አዘውትረው የሚጠቀሙ ከሆነ ቁሳቁሶቹ የሚያመነጩት ጨረር በአእምሮ እድገታቸው ላይ ከሚያስከትለው ችግር በተጨማሪ ለከፋ የጤና ችግር ሊያጋልጣቸውም ይችላል።

6. የአይን መጎዳት

ህጻናት በስከሪን ላይ እያዩ ለረጅም ሰዓት የሚቆዩ ከሆነ ለእይታ ችግር ሊጋለጡ ይችላሉ። ይህም ከሚያነቧቸው ጽሁፎች መጠን ማነስ፣ ለረጅም ሰአት አይንን በአንድ ነገር ላይ በማተኮር እና ከኤሌክትሮኒክሶቹ እስክሪኖች በሚወጡ ጨረሮች/ ብርሀን አማካነት ለአይን ህመም ሊዳረጉ ይችላሉ፡፡

ስለዚህም ህጻናት ልጆችዎ የቴክኖሎጂ ቁሳቁሶች ላይ ረጅም ጊዜ የማሳለፍ ልምድ ካላቸው በአንድ ሰዓት ውስጥ ቢበዛ ለ30 ደቂቃ ብቻ እንዲጠቀሙ አድርጓቸው። በተጨማሪም በቀን ውስጥ በእነዚህ ስክሪኖች ላይ የሚሳልፉት ጊዜ ከ ሁለት ሰአት ባይበልጥ ይመከራል፡፡

Please Share for your Friends

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin
Share on whatsapp