አውሎ ሚዲያ ሙሉ በሙሉ ተመልሷል

አውሎ ሚዲያ ሙሉ በሙሉ ተመልሷል

ሰላም ለናንተ ክቡራትና ክቡራን የአውሎ ሚዲያ ቤተሰቦች ባለፈው ሀሙስ ማታ ግንቦት 12/2013 ዓ.ም የአውሎ ሚዲያ የ ዩ ቱዩብ ቻናል ተጠልፎ ነበር።

ከመጠለፉ በላይ ሙሉ በሙሉ Google ስሙን በመቀየር ከ Google ህጎች ውጭ የሆነ ስርጭት በቀጥታ ከአንድ ሰዓት በላይ በመፈፀም ጎግል ሙሉ በሙሉ አካውንቱ እንዲዘጋው ተደርጎ ነበር።

ይህንን ተከትሎ ከጎግል ጋር ባለን ስምምነት ላይ ተመስርተን በባለሙያዎች በመታገዝ ጎግል በተለያዩ ደረጃዎች ባደረገው ማጣራት

የጎግል አሰራር ሁሉ ታልፎ ተዘግቶ የነበረው የ ዩቱዩብ ቻናላችን ዛሬ ሌሊት ግንበት 15/2013 ዓ.ም ሊመለስልን ችሏል።

ውድ ተመልካቾቻችን የደረሰብንን ችግር በመረዳት በተለያየ መንገድ ስትጠይቁን ብሎም እገዛ ስታደርጉል ለነበራችሁ በመሆኑ አውሎ ሚዲያ ትልቅ አክብሮት አለው።

ባለፉት ቀናት የነበረውን አስቸጋሪ ሁኔታ አልፈን ስራዎቻችንን ሙሉ በሙሉ በተለመደው መንገድ ወደ እናንተ ማድረስ የምንጀምር መሆኑን እናሳውቃለን።

ላደረጋችሁልን ትብብርና ላሳያችሁን ድጋፍ አውሎ ሚዲያ ከፍተኛ ምስጋና ያቀርባል።

Please Share for your Friends

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin
Share on whatsapp