እድሜ እና ቴሌቪዥን የሚያስከትለው የአንጎል ጤና መቃወስ

በቅርቡ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት በ40ዎቹ፣50ዎቹ እና 60ዎቹ የእድሜ ክልል ውስጥ ቴሌቪዥን አብዝቶ መመልከት በቀጣይ የእድሜ ዘመናት ለአንጎል ህመም የማጋለጥ እድሉ ከፍተኛ ነው። ጥናቱ እንደሚለው በዚህ የእድሜ ክልል ውስጥ አብዛኛውን ጊዜያቸውን ቴሌቪዥን በማየት ያሳለፉ ሰዎች በኋላ ላይ በማስታወስ ችሎታቸው፣ በማየት አቅማቸው፣ በማዳመጥ አቅማቸው ላይ መዳከም ተስተውሎባቸዋል። ከዚህም ባሻገር እነዚህ ሰዎች የገዛ ጡንቻዎቻቸውን የማዘዝ ችሎታቸው እና ውሳኔ የመስጠት አቅማቸው ይዳከማል ነው የሚሉት ጉዳዩን ያጠኑት ባለሞያዎች። ይህም እነዚህ ችግሮች ምናልባትም ረጅም ሰዓት ተቀምጦ ቴሌቪዥን ከመመልከት ጋር ተያያዥ ሊሆን እንደሚችል ነው የተነገረው።

የሰው ልጅ አንጎል እጅግ ውስብስብ የሆነ ማዋቅር ነው። ስለዚ ምስጢራዊ የሆነ አካል ገና ብዙ ምርምሮችና ጥናቶች እየተደረጉ ነው የሚገኙት። አንጎላችን በዋነኝነት በሁለት ህብረ ህዋሳት የተገነባ ነው። እነዚህም ህብረ ህዋሳት gray matter እና whiete matter ይባላሉ።

ቴሌቪዥንን አብዝቶ መመልከት በዋነኛነት የአንጎላችን ዋነኛ አካል የሆነውን እና gray matter መጠኑ እንዲቀንስ ያደርገዋል። gray matter የሚባለው የአንጎላችን ክፍል ነገሮችን በማገናዘብ፣በመስማት፣በማየት እና ጡንቻዎቻችንን በማዘዝ ችልሎታችን ላይ ቀጥተኛ የሆነ ተሳትፎ ያለው ።

ምን አይነት ጥንቃቄዎች ይመከራሉ?

የመጀመሪያው የባለሞያዎቹ ምክር በተቻለ መጠን ከሪሞቶ ይራቁ የሚል ነው። ብዙ ጊዜ ሪሞት የመያዝና ቻናል እየቀያየሩ ረጅም ሰዓት ቴሌቪዥን የመመልከት ልማድ ካለ፣ ይህን ልማድ በመጽሀፍ ንባብ እና የእግር ጉዞ መተካት ይመከራል።

እንደው ምናልባት መጽሀፍ ማንበብ ብዙም የማይወዱ ቢሆን ሌሎች አማራጮችም አሉ።

  1. አትክልት መንከባከብ
  2. በቤት ውስጥ መደነስ
  3. ቴንስ መጫወት
  4. ዋና
  5. ገመድ ዝላይ
  6. እንዲሁም ቀለል ያሉ የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ማድረግ ይመከራል።

ማሳሰቢያ! በማንኛውም ሰዓት ሪሞት እጆ ሲገባ ከዛሬ 20 አመታት ብኋላ ስለሚኖሮት የአንጎል ጤና አብረው ማሰብዎን አይርሱ። ከዛ ብኋላ የሚኖረው ውሳኔ የእርሶ ነው።

Please Share for your Friends

Share on facebook
Share on telegram
Share on twitter
Share on linkedin
Share on whatsapp